Office of the Prime Minister

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ወንጀለኞቹን ለሕግ የማቅረቡ ሥራን እቀጥላለሁ ብሏል

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 3, 2021)፦ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ከወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጋር ተያይዞ የተወሰደውን የሕግ የበላይነት ለማዳከም የታቀደ ማንኛውንም ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበል አስታወቀ።

ዛሬ ረቡዕ የካቲት 24 ቀን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ አፈጻጸም ላይ ባወጣው መግለጫ፤ የተወሰደውን የሕግ የበላይነት ለማዳከም የታቀደ ማንኛውንም ጣልቃ ገብነት፤ እንዲሁም በአገርና በመንግሥት ላይ የፖለቲካ ዘመቻን እንደማይቀበል አስታውቋል።

የወንጀል ቡድኑንና ሌሎች ወንጀለኞችን ለሕግ የማቅረብ እርምጃም እንደሚቅጥል ያስታወቀው ይኸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መግለጫ፤ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በሕወሓት ወንጀል ምክንያት ለ30 ዓመታት ብዙ መሥዋዕትነቶች ስለመከፈሉ አስታውሷል።

በትግራይ ክልል የተካሔደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቅ ተከትሎ በክልሉ የተከናወኑትን ዐበይት ክንውኖች እና በአጠቃላይ ከሕግ ማስከበር ዘመቻው ጀምሮ እስካሁን ድረስ ስለተሠሩት ሥራዎች ይኸው መግለጫ በሰፊው አትቷል።

መንግሥት ወደ ሕግ ማስከበር ዘመቻው የገባው በሕወሓት ቡድን አነሳሽነት ስለመኾኑ ጭምር የሚገልጸው መግለጫ፤ ስለሰብአዊ እርዳታ እና መንግሥት ስላከናወናቸው ተግባራት ጭምር በአኀዝ የተደገፈ መረጃ የቀረበበት ነው። የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ቀርቧል። (ኢዛ)

በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ አፈጻጸም ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ

በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ አፈጻጸም ላይ የተሰጠ መግለጫ
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተሰጠው መግለጫ ገጽ 1
በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ አፈጻጸም ላይ የተሰጠ መግለጫ
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተሰጠው መግለጫ ገጽ 2
በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ አፈጻጸም ላይ የተሰጠ መግለጫ
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተሰጠው መግለጫ ገጽ 3

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ