Ethiopia Ministry of Trade and Industry

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

የአውሮፕላን ነዳጅ ከፍተኛው ሲሆን፤ ከአሥር በመቶ በላይ ጭማሪ ተደርጎበታል
ሌሎች የነዳጅ ዐይነቶች ከአንድ ሳንቲም እስከ 17 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጓል

ኢዛ (ቅዳሜ የካቲት ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 6, 2021)፦ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ ተደርጎ ባለፈው ወር ይሸጥ ከነበረው ዋጋ ጨምሮ አዲስ የመሸጫ ዋጋ ተግባራዊ መኾን ጀመረ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከዛሬ ቅዳሜ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ በኾነው የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መሠረት በአዲስ አበባ የአንድ ሌትር ቤንዚን ዋጋ 25 ብር ከ86 ሳንቲም ኾኗል። ኢታኖል የተደባለቀበት ቤንዚን ደግሞ 25 ብር ከ36 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ ደግሞ 25 ብር ከ18 ሳንቲም ኾኗል። ቀላል ጥቁር ናፍጣ ደግሞ 20 ብር ከ27 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 19 ብር ከ78 ሳንቲም ዋጋ እንዲሸጡ ተወስኗል። የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ 38 ብር ከ65 ሳንቲም ዋጋ ወቶለት ከዛሬ ጀምሮ እየተሸጠ ነው።

ዛሬ ተግባራዊ በተደረገው የነዳጅ ዋጋ መሠረት ከፍተኛ የሚባለው ጭማሪ የታየው በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ ሲሆን፤ ባለፈው ወር በሌትር 35 ብር ከ12 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው፤ ከዛሬ ጀምሮ በ38ብር ከ65 የሚሸጥ ይኾናል። ይህም በሌትር ሦስት ብር ከ53 ሳንቲም መጨምሩን ያመለክታል። ይኽም 10.05 በመቶ ጭማሪ መደረጉን ያሳያል።

ከአውሮፕላን ነዳጅ ሌላ በቤንዚን ላይ የ04 ሳንቲም ጭማሪ የተደረገ ነው። ኢታኖል የተደባለቀበት ቤንዚን ዋጋው በተመሳሳይ የ04 ሳንቲም የጨመረ ሲሆን፤ ነጭ ናፍጣ 1 ሳንቲም ጭማሪ የተደረገበት መኾኑን አኀዛዊው መረጃው ያስረዳል። ቀላል ጥቁር ናፍጣ በነበረነት ዋጋ እንዲቀጥል ኾናል። አንድ ሳንቲም የተጨምረበት ከባድ ናፍታ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ