የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች አዲስ አበባ ላይ እየሠለጠኑ ነው
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከኡጋንዳ፣ ከኮሞሮስ፣ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ፣ ከኬንያ እና ከብሩንዲ የተውጣጡ ናቸው
ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. April 12, 2021)፦ የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አባል አገራት ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሥልጠና እየተሰጠ መኾኑን የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አስታወቀ።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከኡጋንዳ፣ ከኮሞሮስ፣ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ፣ ከኬንያ እና ከብሩንዲ የተውጣጡት እነዚህ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች፤ በሰላም ማስከበር ቅድመ ስምሪት ዙሪያ የሚሠለጥኑ ይኾናል ተብሏል።
ሥልጠናው ከዛሬ ሚያዝያ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደሚቆይ ታውቋል።
እንዲህ ዐይነቱ ሥልጠና ለምሥራቅ አፍሪካ የጋራ ሰላም እድገት እና የጋራ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ጌታቸው ሽፈራው ገልጸዋል። (ኢዛ)



