PM Abiy Ahmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

“በምሥራቅ አፍሪካ ይታይ የነበረው በጎሣ ላይ የተመሰረተ ሽኩቻ፤ ከሕወሓት ጋር አብሮ ተወግዷል” ጠ/ሚ ዐቢይ

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 10, 2021)፦ የሕወሓት ቡድን መወገድ ለምሥራቅ አፍሪካ ሰላም ወሳኝ መኾኑንና ይህ አምባገነን ቡድን መወገዱ ለአካባቢው ተስፋን ያሳየ መኾኑን ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክት ሲንዲኬት ለተባለው ድረገጽ በላኩት ጽሑፍ፤ መንግሥት የወሰደው የሕግ ማስከበር ሥራ በሕወሓት አምባገነን ሥርዓት ታስሮ የቆየውን የትግራይ ሕዝብ ከእስር ያላቀቀ ስለመኾኑ ጠቅሰዋል።

በምሥራቅ አፍሪካ ይታይ የነበረው በጎሣ ላይ የተመሠረተ ሽኩቻ፤ ከሕወሓት ጋር አብሮ የተወገደ ስለመኾኑም በሕወሓት ዙሪያ ባሰፈሩት መልእክታቸው ውስጥ ተጠቅሷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ