ዘይት፣ ስንዴ፣ ስኳር፣ የሕጻናት ወተት እና ሩዝ

በፍራኮ ቫሉታ ለቀጣይ ስድስት ወሮች እንዲገቡ የተፈቀዱት መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች፤ ዘይት፣ ስንዴ፣ ስኳር፣ የሕጻናት ወተት እና ሩዝ

የውጭ ምንዛሪ ፈቃድ አይጠየቅም

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. April 15, 2021)፦ በአሁኑ ጊዜ የሚታየውን የሸቀጦች ዋጋ ንረት እና አቅርቦት ለመቅረፍ መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች የውጭ ምንዛሪ ፈቃድ ሳይጠየቅ በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ ተወሰነ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፤ የዋጋ ንረት የመጨመር ሁኔታ እያሳየ በመምጣቱ እና በአቅርቦትና በፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት ያለውጭ ምንዛሪ ፈቃድ መሠረታዊ የሚባሉ ምርቶች እንዲገቡ መፈቀዱን አመልክቷል።

በውሳኔው መሠረት በፍራኮ ቫሉታ ለቀጣይ ስድስት ወሮች እንዲገቡ የተፈቀዱት መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች፤ ዘይት፣ ስንዴ፣ ስኳር፣ የሕጻናት ወተት እና ሩዝ ናቸው።

እነዚህን ምርቶች ለማስገባት ከ250 ሺህ ዶላር ወይም ተመጣጣኝ የውጭ አገር ምንዛሬ በላይ ኾኖ፤ ምንጩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተረጋገጠ እንዲፈቀድ እና ቀረጥና ታክስን በሚመለከትም ማክሮ ኮሚቴው ያስተላለፈው ውሳኔ በአስቸኳይ ተግባራዊ ይሁንም ተብሏል።

የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት በመጋቢት ወር 20.6 በመቶ የደረሰ መኾኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ ከፍተኛ የሚባል የዋጋ ንረት ኾኖ የሚጠቀስ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!