ወ/ት ብርቱካን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
"በሦስት ቀን ውስጥ ቃልሽን አርሚ፤ ካልሆነ እስር ቤት ትገቢያለሽ" ፌደራል ፖሊስ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ታህሳስ 14 ቀን 2001 ዓ.ም. December 23, 2008)፦ የአንድነት ለዲሞክራሰና ለፍትህ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በፌደራል ፖሊስ ተወስደው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ታወቀ።
የፌዴራል ፖሊሶች "በአውሮፓ ሀገራት አድርገሽው የነበረውን ንግግር የሚያስተባብል እርማት ካላደረግሽ፤ ይቅርታ ተደርጎልሽ የነበረው ተነስቶ እስር ቤት ትገቢያለሽ" የሚል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ከአንድ ቀን እስራት በኋላ መለቀቃቸውን ለማወቅ ችለናል።
ሰሞኑን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን በሚመለከት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ የማስፈራራት ዘመቻ የተያዘ ሲሆን፣ ይሄው ዘመቻ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን ለመረዳት ችለናል።