ሁለቱ የቪ.ኦ.ኤ. ጋዜጠኞች ፈቃዳቸው ዛሬ ተመለሰላቸው
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 12 ቀን 2001 ዓ.ም. April 20, 2009)፦ከኢትዮጵያ መንግሥት የተሰጣቸውንና መዘገብ የሚያስችላቸውን ፈቃዳቸውን ተቀምተው የነበሩት ሁለቱ የአሜሪካ ድምፅ ጋዜጠኞች ዛሬ ተመለሰላቸው።
በ1997 ዓ.ም. ምርጫ ወቅት ተቀጥረው ሥራ የጀመሩት ሁለቱ ጋዜጠኞች፤ መለስካቸው አምሃ እና እስክንድር ፍሬው ባለፈው ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. በአቶ በረከት ስምዖን ስር አዲስ የተቋቋመው የመንግሥት ጉዳዮች ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ጠርቷቸው መንግሥት ቪ.ኦ.ኤ. በሚያቀርበው ዘገባ እንዳልተደሰተ ከተገለጸላቸው በኋላ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘገባ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ፈቃድ ቀምቷቸው የነበረ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት እንደተመለሰላቸው የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ጠቁመዋል።