የእነአቶ ተመስገን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ተጠየቀ
Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29,2008)፦ ማህተምና የጽህፈት ቤት መሳሪያዎች አላስረክብም ብለዋልና የነአቶ ተመስገን ዘውዴ ያለመከሰስ የፓርላማ መብት ይነሳልኝና ልክሰሳቸው በማለት አቶ አየለ ጫሚሶ ለፓርላማ ክስ አቀረቡ።
የምርጫ ቦርድ ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲን ለአቶ አየለ ጫሚሶ እንዲሰጥ ከወሰነ በኋላ ማህተምና የጽህፈት መሳሪያ ስላላስረከቡ የእነ አቶ ተመስገን የፓርላማ ያለመከሰስ መብት ይነሳልኝና ልክሰስ ሲሉ አቶ አየለ መጠየቃቸው ታወቀ።
እነ አቶ ተመስገን ዘውዴ በደረሰባቸው ዛቻና ማስፈራራት ምክንያት ማህተሙን ለማስረከብ እንደተገደዱ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።



