በወ/ት ብርቱካን የሚመራው ላዕላይ ም/ቤት ስበሰባውን ለቅዳሜ አዛወረው
Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 28,2008)፦ በተቀዳሚ ም/ሊቀመንበሯ ወ/ት ብርቱካን የሚመራው የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ ሊያደርገው የነበረውን የላዕላይ ምክር ቤት ስብሰባ ለነገ ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2000 ዓ.ም. ማዛወሩን ምንጮቻችን ገልፀዋል።
ትናንት ምክር ቤቱ ዛሬ እንደሚሰበሰብ መዘገባችን አይዘነጋም። (ምክር ቤቱ የሚሰበሰብበትን ምክንያትና ዝርዝሩን አስነብበኝ)



