ማይክል ጃክሰን Michael Jackson (Photo: AFP) 

Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 19 ቀን 2001 ዓ.ም. June 26, 2009)፦ ይህ ዜና ከመፃፉ ከ7 ደቂቃ በፊት የፖፕ ሙዚቃው ንጉሥ ማይክል ጃክሰን በ50 ዓመቱ ኀሙስ ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. (June 25, 2009) ማረፉን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘገበ። እንደ ዘገባው ከሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያለው ስሙ በይፋ እንዳይገለጽ የፈለገና በኦፊሴል የማይክልን ሕልፈተ ሕይወት ለመግለጽ ያልተፈቀደለት ግለሰብ፤ ማይክል ጃክሰን በሎስ አንጀለስ ሆስፒታል ውስጥ ማረፉን አረጋግጧል።

 

የማይክል አምቡላንስ Michael Jackson's ambulance
 የማይክል ጃክሰን አምቡላንስ (ፎቶ ኢ.ቲ.)

የዜናው ትክክለኛነት በብዙዎች ዘንድ ሊታመን ያልቻለ ቢሆንም፤ ሎስ አንጀለስ ታይምስ ዶክተሮችን በመጥቀስ በከተማው ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 9፡20 (3፡20 ፒ.ኤም. / 15፡30) ሰዓት ላይ ሕይወቱ እንዳለፈች ማረጋገጡን በመዘገብ የዜናውን ትክክለኛነት አረጋግጧል።

 

ማይክል ጃክሰን ሎስ አንጀለስ ከሚገኘው ቤቱ 12፡26 ፒ.ኤም. ወደ ሮናልድ ሬገን ዩ.ሲ.ኤል.ኤ. ሆስፒታል ያመራ ሲሆን፣ በወቅቱ የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ የሚሰጡት ባለሙያዎች ሲያገኙት መተንፈስ አቅቶት በኮማ ውስጥ እንደነበር ታውቋል።

 

የዓለም እውቁና የፖፕ ሙዚቃ ንጉሥ የነበረው ማይክል ጃክሰን ጥቁርና ነጭ ህዝቦችን፣ እንዲሁም የዓለምን ህዝብ ለማቀራረብና የሰውን ልጆች እኩልነት በሙዚቃው በመስበክ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት እንደሆነ ይታወቃል። በተለይም ጥቁርና ነጮችን አንድ ለማድረግ በአሜሪካም ሆነ በዓለም ከታገሉት ግለሰቦች ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ይሰጠዋል። ማይክል ጃክሰን በድምፃዊነት፣ በዳንሰኝነት፣ በሁለገብ አርቲስትነቱ የዓለምን ህዝብ ላለፉት 40 ዓመታት ሲያስደስት ኖሯል።

 

ማይክል ጃክሰን Michael Jacksonእ.ኤ.አ. 1982 የወጣው ”ትሪለር” የተሰኘው አልበሙ በፖፕ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ላይ አንደኝነትን እንዳስጨበጠው ይታወቃል። ”ትሪለር” እስከሁን ድረስ እየተሸጠ ያለ አልበሙ ነው።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ