“ፋኖ” ብለን “ሞረሽ” ብለን

በላይ መታፈሪያ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

የዘር ፖሊሲ ጎጠኛ አምባገነናዊነት፣

የወያኔ ግፍ ጭቆና አረመኔ ሥርዓት፣

በወገን ላይ ትልቅ ውድቀት፣

ታሪክ አሳናሽ ከፋፋይነት፣

ጥላቻና መለያየት አጎልብቶ በቅጥፈት።

 

መሰረታቸው ጥላቻ ክፋት፣

ውሸት ከሃዲ ሥራቸው ጥፋት፣

ላቦች አታላይ ሀገር ሻጭ መሬት።

 

“ፋኖ” ብለን እንታገለው በይፋ በተገኘው በአለን ችሎታ፣

ፋኖ ብለን ተባብረንም ተከባብረን በዓመኔታ፣

እናስወግድ በቶል ይህን የወያኔ ዘር በሽታ፣

ለሀገር ለህዝብ ወገን አለኝታ።

 

ሀገራችን ተደፍራለች ህዝባችንም ተዋርዷል፣

ከእንግዲህ በቃን ዝም አንበል፣

“ባገር ወዳድነት” እንነሳ “ሞረሽ” ብለን ይቻላል፣

“ባገር ወዳድነት” እንነሳ “ፋኖ” ብለን ለድል።

 

እናሸብር ጠላትን እናስጨንቅ ዘረኛን፣

እንበትነው እናውድመው ጦረኛን፣

አይደለም ወግ አይደልም ባህል ለህዝባችን፣

በባንዳ ልጅ ፀረ-ሕብረት በጎጠኛ ተገዢነት ለክብራችን።

 

ፋኖ ብለን እንነሳ በጀግንነት፣

ዘረኛ ወራሪን ድል ለመምታት፣

ሀገር፣ ክብርን ላለማስደፈር ነፃነት፣

በተረጋጋ ታሪካዊ ትግል ለመነሳት፣

ሁሉም በአርበኛ ዓይን ሲተያይ በአንድነት፣

 

በጀግኖች ገፀ-ባሕርይ መሪ ተዋናይነት፣

ለእናት ሀገር ኢትዮጵያችን በሕብረት፣

ነው ብሔራዊ ድል መሰረት ለአብነት።

 

“ፋኖ” ብለን እንነሳ ለሀገር ለወገን ነፃነት፣

ለዚያ ትውልድ በውለታ አርበኝነት፣

ለክብር ለሞተልን በጀግንነት፣

ሀገራዊ ወገናዊ በታሪክ ተዋናይነት፣

ኢትዮጵያ ላስገኘልን ላቆየልን በሕይወት መስዋዕትነት።

አልሞቱም ሕያው ናቸው በታሪክ ምሳሌነት፣

ይጠራል ይታወሳል፤ ስማቸው በመልካም አርኣያነት።

 

ምንድነው ዝም፣ ምንድነው ትዕግሥት፣

ምንድነው ችላው አለመቆጨት፣

ይሰማን እንጅ እኛም ወኔ ወንድነት፣

እኛም እንሁን ለኢትዮጵያ ደህንነት፣

በሕብረትም እንታገል ለቀጣይ ትውልድ ዜግነት፣

ይሁን ታሪክ ለዘለዓለም የነፃነት ሐውልት።

ፋኖ ብለን እንነሳ ለሀገር ወገን አለኝታ፣

ለዜግነት ግዳጃችን በአወንታ፣

 

አለ ትውልድ ወደፊትም ጥሩ ነገር የሚሠራ፣

በኢትዮጵያዊነቱ እጅግ በጣም የሚኮራ፣

ያገር ታሪክ የሚያራምድ፣

የመልካም ሥራ ቀጣይ ትውልድ፣

ለእናት ሀገር ለኢትዮጵያ

ነውና ታሪክ ለሰው ልጅ መኩሪያ።

 

ፋኖ ብለን እንነሳ ለሀገር ወገን አለኝታ፣

ለዜግነት ግዳጃችን በአወንታ፣

ባገር ወዳድነት እንነሳ “ሞረሽ” ብለን ይቻላል፣

ባገር ወዳድነት እንነሳ “ፋኖ” ብለን ለድል።


 

ተፃፈ በበላይ መታፈሪያ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ