“ልቤ እንዳታዝን” (በላይ መታፈሪያ)
“ልቤ እንዳታዝን”
በላይ መታፈሪያ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
እኔ እናታችሁ፣
እናንተም ልጆቼ ናችሁ፣
እኔና እናንተ አንድ ነን፣
የምንኖር አንድ አካል ሆነን፣
ብዙ ሺህ ዓመታትን ያስቆጠርን፣
የቆየን ያለን፤ ሁሉንም በግረን ይዘን።
የናንት ታላላቅ ልጆቼ፣
በመልካም ተንከባክበው ጧሪዎቼ፣
ለዚህ አበቁኝ ለዚህ ሰዓት፤
እንድሆን የእናንት እናት።
እኔም በእናንተ እመካለሁ፣
እናንተንም ወልጃአለሁ፣
እጅግ በጣም እኮራለሁ፣
ልጆቼ ሀብቴ ብያለሁ፣
ከእንግዲህ በእናተ ነው መንከባከቡ ተስፋዬ
ቢደክመኝ፣ ቢያመኝ፣ ባረጅ ጧሪዬ።
ይኸው ደከመኝ በሽታ ያዘኝ፣
አሁን ልጆቼ ድረሱልኝ፣
ሳይጠናብኝ በሽታው፣
የያዘኝ የዘር መጋኛው፣
ኑ ሁላችሁም በአንድነት፣
እኔን “እማማ” ብላችሁ እናት፣
ተጠራሩ በቶል ኑልኝ፣
ሳይውል ሳያድር “አለን!” በሉኝ።
ተረዱልኝ ይህን በሽታ በእውነት፣
ይመስለኛል መርዘኛ ከፋፋይም ሰውነት፣
የሚያዳክም ቀናሽ ጉልበት፣
ይሉታል የወያኔ ወረርሽኝ፣
እባካችሁ ኑ በቶል ድረሱልኝ፣
ማሳከኩ ሳይጠናብኝ፣
ሕመም አለው የሚቆረጥም፣
ከእራስ እስከ ጥፍሮችም፣
እግር እጄን ሽባ አድርጎ አንቆ ይዞኝ፣
ሳይቆራርጥ አካሌን ልጆቼ ድረሱልኝ።
ዝም አትበሉ ዳተኛ፣
እንዳልሆንም ብቸኛ፣
ልቤ እንዳታዝን በናንት፣
አስታማሚ አጥቼ የብዙ እናት፣
እንዳልሆንም መሳለቂ በጎረቤት ጠላቶች፣
የወላድ መካን እያሉ ሆነች።
ኑ ልጆቼ ተስፋዎቼ ልበላችሁ፣
መድኃኒቱን ሐኪሙንም ይዛችሁ፣
ሁላችሁም በአንድነት አለን በሉኝ፣
ከዚህ ወያኔ የዘር በሽታ ደዌ አድኑኝ።
ልቤ እንዳታዝን፣
በሉኝ አለን፣
ኩሩ በታሪክ በነፃነት፣
በጋራ ሕብረት በእኩልነት።
በላይ መታፈሪያ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.