እስረኞች (በፈቃዱ ሞረዳ - ስለቴዲ አፍሮ)
እስረኞች
በፈቃዱ ሞረዳ (ስለቴዲ አፍሮ)
ምንድነው ጫጫታው፣ ሆይ ሆይታ ቱማታ?
“እገሌ ነፃ ነው፣ እንትና ተፈታ”
ጎበዝ ረጋ በሉ፣ ሠርክ አትሳሳቱ
ማንም አልተፈታም፣ ሙሉ ነው ’ስር ቤቱ።
በዘብጥያው መሃል ልዩነቱ ያለው
አንደኛው መጥበቡ፣ ሌላው መስፋቱ ነው።
“እገሌ ተፈታ፣ እገሊትን ፍቱ!”
እናንት “እስረኞች” ቧልት አትፎትቱ።
ባፀደ ጠብመንጃ በታገተች ሀገር
“ፍቺ” ብሎ ቆሳ፣ “ነፃ” ብሎ ነገር።
ወጪና ገቢውን ይቅር አትቁጠሩ
የተኛው ይቀስቀስ፣ ላልሰማው ንገሩ
ትጉ ለተባብሮ፣ አፀዱን ስበሩ።
በፈቃዱ ሞረዳ (ስለቴዲ አፍሮ)