ለብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የ፵ ቀን መታሰቢያ

አቤል አድማሱ

ሰው ጠፍቶብኝ ስባዝን

ተወዳጁን ወገኔን

የኦርቶዶክስ ጠበቃን

የሀገር ቅርስ አቡኑን

የትህትናው አባቴን

ምስክሬ እድገቴን

ኢትዮጵያዊው አድባሬን

ዜና ማርቆስ ታላቁን

ባለ ማዕረግ ጳጳሱን

ከላይ ከታች ባዘንኩና

ላላገኘው እንደገና

ተስፋ ሳልቆርጥ እንድፀና

ያንን መልካም ባለዝና

አባታችን ወዴት ነህ?

ዜና ማርቆስ ወዴት ነህ?

ብንመጣ ያጣንህ

አልነበረም ልማድህ

ሰው ሲመጣ መሸሽህ

ጤና አጥቷል ብለውኝ

ይማር ብዬ ማለድኩኝ

አሁንማ ፈራሁኝ

ዝም እንዳልል ባባሁኝ

ለካ እውነት ነው መጥፋትህ

ውሎ አድሮ መሄድህ

ሰው ነህና ደረሰህ

ተስፋ ቆረጥኩ ከእንግዲህ

ዜና ማርቆስ ታላቁ ሰው

ትህትናን ያስተማርከው

መልካም ትምህርት ያበሰርከው

ዜና ማርቆስ የወንጌሉ

መምህራችን ርዕቱ ቃሉ

ተባረክን በመስቀሉ

ተፈወስን በፀበሉ

ቀድስልን እባክህ

ስበክልን እባክህ

አስተምረን እባክህ

ዜና ማርቆስ ባባትህ

በአዛኝቱ በናትህ

አንተማ ሄድክ እንደዋዛ

ሀዘናችን በጣም በዛ

አንተማ ሄድክ በቀላል

አንጽተኽን ከበቀል

እግዜር ያጥናሽ ኢትዮጵያ

አጣሽ አሉ ሐዋርያ

እግዜር ያጥናሽ ተዋኅዶ

ሊቅ ሞተብሽ በተለምዶ

እግዜር ያጥናህ ሉቃስን

ዮሐንስን አቡኑን

ካህናትን ምዕመናን

አትቀስቅሱት ያንን ሰው

ጸሎት ምልጃው ለኛ ነው።


የአባታችን በረከትና ጸሎት በሁላችን ላይ ይደርብን!

አቤል አድማሱ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ