እንበል አስራ ሰባት*

ከእንቆጳ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ከጨለማው በስተጀርባ

ከድቅድቁ ብርሃን አልባ

ከጣይቱ መውጫ ማዶ

ሰው አየሁኝ ዛሬ ማልዶ።

የጥቁር ዘር አፍሪቃዊ

የኩሽ ቅሬት ነባራዊ

የበቀለው ካገሬ-አፈር

የሜቶ ልጅ የብርቱ ዘር።

እንደተወጣው ሽቅቡን

የቅኝ ግዛት አቀበቱን

አባ ዳኘው ዛሬም ከርሞ

ሞተ ስንል ነቃ ደግሞ

ስብዕናን አገልድሞ።

የወንዜ ልጅ ጊቤ-ባሮ

የአኟክ ፍሬ ከኩሽ ጓሮ

ዛሬም ያፈራል ደግ-ደጉን

የምዬ ሆድ ወንድም ክንዴን

ሩቅ አላሚ አሳቢዋን እታለምን።

ታየ! ሰው ታየ! ከዚያ መንደር

ለወገን ስንቅ ጥላ ላገር።

ፍትህ ናፍቆት እንደብርቱ እንደህቱ

ፍቅርን ሰብኮ በጠዋቱ

አለ ዘሬን ከስር ፍቱ!!


*ሰሞኑን በአቶ ኦባንግ ሜቶ አማላጅነት ከጃፓን እስር ቤቶች ለተፈቱት 17 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን፤

ከእንቆጳ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ