የኑሮ ማስታወሻ (አስራት አብርሃም)
የኑሮ ማስታወሻ
አስራት አብርሃም
1
ድሮ
ሜርኩሪ ነበር
በደላላ ሳይቀር
ባገር ሚፈለገው፤
ብልሁ መሪ ዛሬ
በሃያ ዓመቱ
የመብሉን ዘይት
ሜርኩሪ አደረገው።
2
በደህናው ጊዜ
ስኳር የቀመሱ፣
ዝቀው ያስቀመጡ፣
ምንኛ ታደሉ፤
ዛሬ!
ስኳር የጠፋለት
ያኔ ካስቀመጡት ዝቀው ይቅማሉ።
አስራት አብርሃም This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
16/09/2003 ዓ.ም.



