ጀግና መካሪ

አርባምንጭ

ከጉዋደኛዬ ዱር አድረን

ውድቅት ጅብ ሲያንኮሻኩሽ፣

ምንድነው እሱ ብለው

ዝግ ባለ ድምፅ በትንሽ፣

ዝም ብለህ ተኛ አንተ ሰው

የባሰ ነገር አታምጣ፣

ጅቡ እገሬን ጨርሶ

ወደ አናቴ እንዳይመጣ፤

ብሎ መከረኝ ወዳጄ

ጀግና መካሪ አይጥፋ፣

እያየ እግሩን አስረክቦ

ለተረፈው እሚለፋ።


አርባምንጭ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ