እሱም እንደእናንተው ከያኒ (ቱሉ ፎርሳ)
እሱም እንደእናንተው ከያኒ
(ቱሉ ፎርሳ ከነምሳ)
ለእሱም ጥበብ እኮ ናት አድባሩ
የመንትያ ነፍሱ ፍቅሩ።
እሱም ይወዳል ፈጠራ
የ99.6% ድል ጭፈራ
11% ዕድገት አዝመራ
ምናባዊ ሴራ።
እሱም ጫታም ነው
ጉንጭ አልፋ፣
ህይወቱን አዝላቂ በቀፈፋ።
እሱም ያመልካል እራሱን
መስማት ይወዳታል ድምፁን።
ልዩነታችሁ ግና
አንድና አንድ ብቻ፣
እሱ ደም ሲያፈስ የምር ነው
ቀይ ቀለም እይደል እንደእናንተው።
ከዚህ በቀር አንድ ናችሁ
እሱም አለው ሠራዊት
የእናንተም እስትንፋስ ሠራዊት
በየራሳችሁ መንገድ አራዊት።
እሱም ጥበብ እኮ ናት አድባሩ
የመንትያ ነፍሱ ፍቅሩ።
እሱም ጥበበኛ
ብሄረ ፈጠራ
የ99.6% ድል ጭፈራ
11% ዕድገት አዝመራ
ምናባዊ ሴራ።
(ቱሉ ፎርሳ ከነምሳ)
ለመለስ ዜናዊና ለሠራዊት ፍቅሬ ሠራዊት



