እነሆ

አርባምንጭ

እምጽፍልሽ ቅኔ፣ እማራቅቀው ክታብ፣

እማሰማልሽ ዜማ፣ እማሳምረው ንባብ፣

እምጠራልሽ ደብተራ፣ እማስጠነቁለው ትብታብ፣

ደዌሽን ካልመነገለ፣ ነቀርሳሽን ካልነቀለ፣

የተጣባሽ ዛር ለምሱ፣ የልጅሸን ደም ካለ፣

እንደ ክርስቶስ ልሙት፣ ልሰቀል ልገረፍና፣

እነሆ ደሜ ለክብርሸ፣ አጽሜም ላንች ልዕልና፣

እንጅ ከንፈር ምጥጬ፣ አላዳንኩሽም እናቴ፣

አልረባሽም ረጅም ዲስኩር፣ እሚጣፍጥ አንደበቴ

አልጠገነሽም ማስመሰሌ፣ አልከለለሽም ፍርሃቴ፣

ቆፍጠን ብዬ ካልለወጥኩት፣ ሕይወት ፈውስሽን በሞቴ።


አርባምንጭ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ