ከኮረጁ አይቀር 

ቱሉ ፎርሳ ከነምሳ

ከሰረቁ አይቀር፤ ከሰው ጋን ከቀዱ

ሠላም ዲሞክራሲን፤ ምነው በኮረጁ!

ምነዋ ሸጋውን፤ ከሰው ደጅ ባፈሱ

ትሩፋቱ እንዲተርፍ፤ ለአገር ልጅ በሙሉ?

ምነው በኮረጁ፤ ከሰው ግብር ሰናዩን

ፍትህን ርትዕን፤ ፈሪሃ እግዚአብሔርን?

ከሰረቁ አይቀር፤ ከሰው ከጨለፉ

ሰብዓዊ አመራርን፤ ምነው በኮረጁ

አፈናን ኮንነው፤ ፍቅርን በለፈፉ!

 


ቱሉ ፎርሳ ከነምሳ

ለአምባሳደር ተስፋዬ ሃቢሶ እና ”በእንባ አሳድር” አለቆቻቸው

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ