የኔሰው ነደደ!

ወርቅእሸት ቸርነት

የደብረ ሊባኖስ ገዳሙ ሲቃጠል፣

ካህን እሳት ገብቷል ለእምነቱ ሊጋደል፤

የዚያን ጊዜ መሪ ንጉሥ ልብነ ድንግል፣

ጠፍታ አገሬ ከማይ እኔ በፊት ልጥፋ፣

በማለት ቃል ገብቶ በረሃ ላይ ሞቷል፤

ልጁ ገላውዲዎስ ጠላትን አጥፍቷል፤

ከፋ ኩሎኮንታ የጎጀብ ጋብቻ፣

በደቡብ ኢትዮጵያ ኦሞ ወንዝ ዳርቻ፣

የዳውሮ አስተማሪ የዋካ ጉትቻ፣

የኔሰው ነደደ የኢትዮጵያ ቶክቻ፤

ራስክን ያቀረብክ መስዋዕት ለሕዝብ፣

የዘመኑ ጀግና የኔሰው አቤት! ልብ፣

“ዋካ” “ብርሃን” ነው በቃል ትርጉም መፍቻ፣

ብርሃን ለኢትዮጵያ ዳር-እስከዳርቻ፤

አላውቅህ አታውቀኝ የሩቅ- ለሩቅ ሰዎች፣

ኦሞ ከአባይ ሲደርስ የ-አንድ ወንዝ ልጆች፤

የጠጣነው ውኃ ያገር ልጅነቴ፣

በእሳት በመንደድህ ተቃጠለ አንጀቴ፣

ሞሃመድ ቦዚዚ የቱኒዚያ ሰው፣

ራሱን አቃጥሎ ወገኑን ፈወሰው።

ሊቢያና  ግብጥን ሁሉን አደረሰው

ለኢትዮጵያ አርነት ተቃጥሏል የኔሰው።

እሳት የሚጨብጥ ጀግና የጦር መሪ፣

ገበየሁ የሚሉት ባለ ልዩ ሱሪ፣

ታሪኩን ዝናውን ስሰማ ሳወራ፤

የኔሰው ተገኘ በዘመኑ ተራ፤

የራሱን ፈፀመ የአያቱን አደራ፣

ኢትዮጵያን ለማዳን እንሙት በተራ።


ለየኔሰው ገብሬ

ወርቅእሸት ቸርነት

ህዳር 2004

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ