ለማሞ ውድነህ (ክንፈ ሚካኤል)
ለማሞ ውድነህ
ክንፈ ሚካኤል
ለማሞ ውድነህ ላንጋፋው፣
ለደራሲና ለጋዜጠኛው።
ማሞ ወዱ፣
ድርሰት ጋዜጣ ግዱ፣
ኢትዮጵያ ናት ዘመዱ።
ጋዜጠኛና ደራሲ፣
ደራሲና ጋዜጠኛ፣
የቱ ይቅደም የቱ ይከተል.
በሙያ ተርታ ሲተካከል።
ሁለቱም ለሱ አንድ ገጽ ነው፣
በድርብ ሙያ የተካነ ነው።
እኔም ሀዘኔን ልወጣው፣
ድርሰት ጋዜጣውን ላንብበው።
ማሞ ውድ ነው ላገሬ፣
ላፍስ እንባዬን አምርሬ፣
አይወጣልኝም ተናግሬ።
ደሞም ላጽናና ቤተሰቡን.
እግዜር ይጠብቅ ነፍሱን።
ያገሬ ጠበብት ተራ በተራ፣
እየለቀቁ ያለ አደራ።
መጨረሻዋ ምን ይሆን፣
እንደ ደመና መበታተን።
ክንፈ ሚካኤል
ወርሃ የካቲት ፳፻፬ ዓ/ም
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.