ዕንባዬን አፋልጉኝ

ቅዱስ ያሬድ (Norway)

ያኔ የዛን ግዜ

ሀገሬ እያለው በኖርኩበት ግዜ

ምንም ሳይጎድልብኝ ሁሉንም አግኝቼ

ፍቅር እና ሰላም ጨዋታን አግኝቼ

አነባው ነበር የውስጤ አውጥቼ

ምንም ሳይደርስብኝ እንደው ተደስቼ።

 

 

ዛሬ ግን ቢከፋኝ ሁሉ ጨልሞብኝ

ቋንቋና ባህሉ አዲስ ቢሆንብኝ

የሀገር የወገን ናፍቆት ቢብስብኝ

እንዳሰብኩት ሳይሆን ሌላ ቢሆንብኝ

ማልቀስም አቃተኝ ዕንባዬም ጠፋብኝ

ወገን ለመቼ ነው ...

ለዛሬ ያልሆነኝ?

ዕንባዬን ፈልጎ ውስጤን የሚያብሰኝ።


ቅዱስ ያሬድ (Norway)

 

12/03/12

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ