ንዲህ ነዋ!*

ገ/ኢ. ጎርፉ

ከውጭ፣ ከውርጭ ቤት ሲገቡ

ሙቅቱ፣ ስሜቱ

እንዴት ነው ቢሉሽ - ትርንጎውን

ትንፋሽሽ በሮማን ከንፈርሽ 

እፍፍፍ ... በዪባቸው

አትፍሪ፣ አትፈርያቸው

“እንዲህ ነዋ!” - በያቸው።

 

 

የዓጋሙ፣ የቀጋው፣ የአደሱ፣ የጥሪኝ

መዓዛው፣ ሽታው

እንዴት ነው ቢሉሽ - ጋሜሽን

ግለጭው፣ ሽሩባሽን ፍቺው …     

አሳዪአቸው…

አትፍሪ፣ አትፈርያቸው

“እንዲህ ነዋ!” - በያቸው።

 

ጨረቃ ብቅ ስትል ከዳመና ውስጥ

ብርሃንዋ፣ ድምቀትዋ

እንዴት ነው ቢሉሽ - መቀነትሽን

ፍቺው፣ አውልቂው ልብስሽን ...

አሳዪአቸው …

አትፍሪ፣ አትፈርያቸው

“እንዲህ ነዋ!” - በያቸው።

 

የሱስ ሙታንን ያስነሳው

በረቂቁ  ታምር

እንዴት ነው ቢሉሽ - ጠጋ  በዪኝና

ከንፈሬ ላይ ሳሚኝ - ፍቅርሽን

አሳዪአቸው …

አትፍሪ፣ አትፈርያቸው

“እንዲህ ነዋ!” - በያቸው።


 ገ/ኢ. ጐርፉ

 

 * ዝክረ ሩሚ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ