ሄደች አሉ ሄደች፤ እንደወጣች ቀረች

ላታይ ወደሗላ አሻፈረኝ አለች፣

‘ልጆቼ ተርበው አይኔ ከሚያይብኝ

ምስቅልቅል ሀገሬን ተመልሸ ከማይ

ድህነት፣ ርሀብ፣ ብድርና ስቃይ

ከሚያንከራትቱኝ ከታችና ከላይ

እዚሁ አለሁበት ከአረቦች ሀገር

አረቦቹ ምድር

ሬሳየ ወድቆ በሜዳ ላይ ይቅር።’

ብላ ትታን ሄደች::

የሗሊትን ትታ ወደፊቷ አመራች

አንድ ሞትን መርጣ

ሁለት ሶስቱን ተወች።

 

(ለአለም ደቻሳ) march 17/12

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ