ምን ይሻለኛል? (ገ/ኢ. ጐርፉ)
ገ/ኢ. ጐርፉ
አንዳንዴ ይገርመኛል፣
ግራም ይገባኛል፣
ጉልበቴ ይዝላል፣
ሁለንተናዬ ይሰንፋል፣ ይዝለፈለፋል፣
ነፍሴ ይሸበራል፣
ጭንቅ ይለኛል!
አካላቴ ይደክማል፣ ይላሽቃል፣
ቅጡ ይጠፋኛል፣
አዕምሮዬ ይበሳጫል፣ ይበሽቃል፣
መንፈሴ ይረበሻል፣
ጥፋ! ብረር! ይለኛል፣
ፈዝዛል፣ ይላሽቃል፣
መንፈሴ ይረበሻል፣
አዕምሮዬ ይበሳጫል፣ ይበሽቃል፣
ጥፋ! ጥፋ! ይለኛል …
ምን ይሻለኛል?