አሜሪካ! አሜሪካ! (ገ/ኢ. ጎርፉ)
ገ/ኢ. ጎርፉ
ፈጽሞ ሳልረሳው ኢትዮጵያዊነቴ፣
የተቀበረበት የሕፃን እትብቴ፣
እስቲ ላንጐራጉር ስለ እንጀራ እናቴ፣
አንዴ ላሞጋግስ አሜሪካነቴ ...
ዓለሙን በሙሉ በምግብ ሲረዳ፣
ማንስ ግድ ብሎት፣ ማን ጥሎበት ዕዳ?
"ዘረኝነት አለ፣ ቀይ/ጥቁር አለ!"
ለሚባለው ወሬ፣ ወዴት ነው የሌለ?
የዓለም ስደተኛን ሰብስቦ፣ አስጠግቶ፣
ቅቤ፣ ማር ፈትፍቶ፣ አብልቶ፣ አጠጥቶ፣
በሰላም ሲያኖረን እኩል መብት ሰጥቶ፣
እንዲህ ያለ ሀገር አይታወቅ ታይቶ...
እስኪ ማን አለና እንደ አሜሪካ
በጥበብ፣ በዕውቀት ሞያን የሚያሳካ፣
ወደ ህዋው መጥቆ ጨረቃን የነካ፣
በሃብትም ብርታትም አንጀት የሚያረካ...
አሜሪካ አገሬ ኑሪልኝ ቆመሽ
አንድ-አንድ ስሕተቶችን የምጠቁምሽ
እንድትደምቂልኝ ሁሉን አርመሽ፣
የፍቅር ነው እንጂ፣ አይደል ጠልቸሽ።
የዕለትን ጥቅም ወደ ጐን ትተሽ፣ ? ?
ሐሰትን፣ ሽንገላን ሰርክ አስወግደሽ፣
ቁሚ ለእውነቱ በሐቅ ጸንተሽ፣
እስተ ዘልዓለሙ እግዜር ይባርክሽ።
ገ/ኢ. ጐርፉ



