ገ/ኢ. ጐርፉ

ብዙ የሰው ልጆች የተካኑት መላ

ሊቃውንቶች መስለው መታየት በሌላ

ራሳቸውንና ሰውን ሲያታልሉ

ጠምጥመው፣ አጊጠው፣ አለን! አለን! ሲሉ

አዋቂ ከመሆን መምሰል ነው ቀላሉ ...

በእንስሳትና ጥቃቅን ፍጥረት

አደገኛ መስሎ ለማስፈራራት

እጅግ ጠቃሚ ነው መስሎ መታየት።

ግን ጠላት ጨክኖ የመጣ ዕለት

መስሎ የቆመ ሰው ወዮው! ውዮውለት!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ