ወለላዬ (ከስዊድን)

(ግጥሙን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

Prof. Mesfin Woldemariam. ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ሰው በሕይወት ሳለ መቼም ማድነቅ አንወድ

ማሻሻል አለብን ይሄን ነገር የግድ

እኚህ ጠንካራ ሰው ፕሮፌሠር መስፍን

ለራሳቸው ቢሆን የለፉት እስካሁን

ሀብት ከሥልጣን ጋር በእጃቸው ጨብጠው

በታዩ ነበረ ከሁሉ ሰው በልጠው

ነገር ግን እኚህ ሰው ለሀገር ሲለፉ

ምንም ሳይኖራቸው ዕድሜአቸውን ገፉ

ሆኖም እንደሳቸው ከህሊናው አድሮ

መኖር ክብር አለው እየበሉ ሽሮ

ጥንትም ሆነ አሁን በተሳሳተ ሀገር

መቼም ድኖ አያውቅም አዋቂ ከችግር

ገዢን የማይፈሩት በዕድሜ ዘመናቸው

እኮ ለምንድነው ብለውም ቢሏችሁ

ህሊናው የጸዳ ያልፈጸመ በደል

እስከዛሬ ድረስ መቼ ፈርቶ ያውቃል

ብላችሁ መልሱ ይሄን ተናገሩ

ሌላ ምንም አይደል አትጠራጠሩ

እኚህን ታላቅ ሰው እንያዛቸው በወግ

በዕድሜ ዘመናቸው ክብርን አንንፈግ

የሳቸው ብቸኛ ህዝብ ነው ሿሚያቸው

ማዕረጋቸው ላይ ማዕረግ እንስጣቸው

******

ለፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም 86ኛ የልደት በዓል መታሰቢያ የተጻፈ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ