አምባሰል

ክንፈ ሚካኤል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ከፉከራም አልፎ ስንት ያውቃል አምባሰል

እጅ አልሰጥም ብሎ ማርኮም ግዳይ መጣል።

እየጠበቀ እንጂ ዛሬ ነገ እያለ

መተኮስ የሚሻ በየቤቱ ስንት አለ።

ወያኔ እንደ ትል ነው መሀሉን ይበሳል

ሰርስሮ ሰርስሮ ወናውን ያስቀራል።

ደርግ ፋሽስት ነው ከወያኔ አይከፋም

ሥልጣን ቢጥመውም ሀገር አያጠፋም

የወያኔ ግፉ በጣም ይከረፋል

ሳይፎክር ሳይሸልል

እጅ እግር ይቆርጣል።

ፋሽስትም ደግ ነው ከወያኔ ቢሉ

በጠራራ ፀሐይ ሰው እየገደሉ

የፍየል ወጠጤ ሲሉ ይሰማሉ።

ወያኔ ጭካኔው እጅጉን ይብሳል

ገሎ በልቶ ቀብሮ አብሮ ያላቅሳል።

ክንፈ ሚካኤል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ሜልበር፣ አስትራሊያ

ግንቦት ፳፰ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ