ለእልፍ - አዕላፍ ግፉዓን (ጌታቸው አበራ)
ትውስታ - ወቴዲ-ብርቱካን
ለእልፍ - አዕላፍ ግፉዓን
ጌታቸው አበራ ሰኔ ፪ ሺህ ፩ ዓ.ም. This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
በሸፍጥ፣ በተንኮል፣ በቂም ... ተበክለው፣
በጥላቻ፣ በሃኬት፣ በበቀል ... ተሞልተው፣
እልፍ-አዕላፍ ፍቅር መሸከም አቅቷቸው።
ተፈጥሮ ቀምማ - በቸረችው ጥበብ፣
“ነፍስ” ሊዘራበት - ተስፋ አጣውን ህዝብ፣
ቅኔውን አሳክቶ - ሙዚቃ ቀምሮ፣
በየሰዉ ልብ ውስጥ - አምነቱን አኑሮ ...፣