የጥዋት ቃል (ብርዞ)
የጥዋት ቃል
ብርዞ ከፍራንክፈርት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
በቅባት በርቶ ፊቱ
ተስሞ ጉንጩን በእናቱ
ቁንጮው ተበጥሮ ወደላይ
ሲኩዋትን ለትምህርት በዝላይ
ደርሶ ሲሰለፍ በቁመቱ
ቃል ሊሰጥ ለሀገሩ በጥዋቱ
ወደ ባንዲራው በፍቅር አንጋጦ
ሲዘምርለት በስሜት ተውጦ
አረንጓዴ - ቢጫ - ቀዩን ቀለም
አጥንቱ የገባ የተዋሃደ ከደም
ከልጅነት እስከ ዕውቀት
ኢትዮጵያን በአንድነት ማቆየት
የትውልድና የታሪክ አደራ
ሊወጣ ለነፍሱ ሳይፈራ
በአደባባይ በጥሻ ዱር ገደሉ
ለልዕልናዋ ያለፉ ያሉም በትግሉ
የጠዋቱን ቃል ያከበሩ
በባንዲራችን ዘለዓለም ይዘከሩ
ብርዞ ከፍራንክፈርት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.