ጳጳስ

ቦጋለ ዳኜ ከካሊፎርንያ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

ጳጳስ እህል ይጥም እንጀራ ይበላ

በማይመስልበት ምድር በጦብያ በሞላ

የስድቡ ሲደንቀን ተቃጣበት ዱላ

በምጡ ዋዜማ እንጃ ካሁን ሁዋላ።

 

መስፍን ዘውድ ሊጭን ቄስ ዲያቆን ሊካን

እንዲህ በቀላሉ መች ተገኝቶ አቡን

አቡኑን ፍለጋ ሲጎርፍ ከያቅጣጫው

ስንቱን ደራሽ ውሃ አዞ እንዳልጨረሰው

በትረ ቃየል ሰጡት በትረ ሙሴን ትተው።

 

በ1940ዎቹ መጀመርያ በርካታ ጳጳሳት በመሾማቸው በጊዜው የነበረውን ደስታ ለመግለጽ፤ ስሬ መድኃኔዓለም ላይ በዓለ ሲመተ ጵጵስና ሲከበር፤ የታወቁት የቅኔ መምህር አለቃ ጥበቡ ገሜ የተቀኙትን መወድስ እስቲ እንመልከት። ቅኔውም ይመዘገብላቸው።*1

 

*1መወድስ

“ይቤ ባስልዮስ በከመ ፈቀደ

ኃይለሥላሴ ይገብር ወዘከም ሀለየ ይፌጽም፤

አምጣነ አልቦ ዘይብሎ እምነገሥተ ኩሉ ዓለም

ዘንተ አህሰምከ።

ምክሩስ ለኃይለሥላሴ ነገዱ ለሴም

ይሄሉ ለዓለም።

ወኢይትቃወሞ በግብር መንበረ ዓመፃ ከዓዌ ደም።

 

ወቆሙ ጳጳሳት አእማደ ሠላም፤

ኢትዮጵያ ማእከሌኪ በየማን ወበጸጋም።

ወአመ ይዌውኡ ጸር ውሉደ መርገም፤

ኢታርምምኬ አልጋ ወራሽ ወልዑል መኮንን ኢትጸመም።

 

ጥበቡ ገሜ ዘስሬ መድኃኔዓለም (ሥላሌ)

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ