መታፈር በከንፈር

የካናዳው ከበደ

እስቲ ምን ይባላል ያሁኑ ክርክር

መሆኑ ቀረ ወይ መታፈር በከንፈር

ሁሉን ነገር አይቶ ተናግሮና ሰምቶ

ሠላምን በመፍጠር ነገር አረጋግቶ

እውነትን ይዞ ሲገባ መሄድ

አንተ አንቺ ብሎ አውርዶ መውረድ

መጥፎ ቢሆንም ሚከፋው ይበልጥ

ፀጉር ሲነጣ ሲመስል ነው ጥጥ

ዋሽቶና ቀጥፎ ሥልጣን ለመያዝ

መሯሯጥ መሄድ በጭፍን መጓዝ

ግቡን አይመታም ከንቱ ነው መና

ጉም መጨበጥ ነው መዝገን ዳመና

ጥንትም ድሮም አለ በሰው ልጅ ላይ ድክመት

በጥፋቱ ወቅሰው ካላስተካከሉት

እንደው ይሄም ባይሆን ሁሉም ባይሰምርልን

ወግና ልማዱን ባህሉን ምን ነሳን

ዲሞክራሲም ቢቆይ ትግሉ እስቲጠነክር

መሆኑን አትርሱ መታፈር በከንፈር።


 

የካናዳው ከበደ 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ