ኡ … ኡ … ታ! ናፈቀኝ

(አባ ቤክሲሳ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

‘ወንድ’ ይወጣኝ ብዬ

ትንፋሼን ሰብስቤ

ቀበቶዬ ጠብቆ

ጀግንነት ደርቤ

 

አምባው እንዲረበሽ

ባየሁት አበሣ

ብሶቴ እንዲሰማ፤

እሪታየን ላቀልጥ

ላምቧርቅ ስነሣ

 

የሆዴን መራቡን

አጯጯሄን ንቀው

ጮኸው ሊያጯጩኹኝ

ምለው ተማምለው

ደቦ ተጠራርተው

ሥልጣን ተመራርቀው

 

ሊታደጉኝ ነው ስል

ካሣር ከመከራ

ዳግም ተከፋፍለው

ለስሜ ስም ሰጥተው

ጩኸቴን ቀምተው

ኡ! ኡ! ይሉብኛል

ኡኡታዬን ነጥቀው።

 

መቸስ ምን ይደረግ!

እንደኔ የከፋው

ሆድ የባሰው ባገኝ

አልቀረውም ነበር

እሪ … እንደናፈቀኝ።


 

አባ ቤክሲሳ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ