እውነት

ወንድወሰን ሰብሰቤ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

ሐቅን ስትናገር የኖረች አንደበት

መጽሐፍ ተገልጾ የተነበበበት

ኑፋቄ አመጡብን ሊቁ በሌለበት

እራስን ማዳን ነው ጊዜው አስፈርቷል

ሳይነጋ ሊመሽ ነው ሊቁም ሄዶ አልቋል

ልብና አንደበት ጥፋቱን አቅርቧል

ውሻው ተመሳስሎ ከሰው መሃል ቆሙዋል

 

ንገሩን እውነቱን የቱ ነው መንገዱ

መኮብለል ይሻላል እናንተ ሳታብዱ

ከናንተ ብንቀድም ካልቀረ መሄዱ

 

ተሰቀለ ሞተ ያላችሁት ሁሉ

ልትደግሙት ካልሆነ ዳግም በመስቀሉ

ስህተት ኖሩዋል ለካ እናንተን ማብቀሉ

 

ህሊና ካላችሁ ዛሬም ተመለሱ

ተናግራችሁ እለፉ እውነቱን መልሱ

ትምክህትን አውጡት ሳይመጣ ንጉሡ

 

ውሾቹን ወስዳችሁ ከቦታው እሰሩ

ልትሄዱ ነውና ልትገቡ ካፈሩ

እውነት ሳይመለስ በመላ ሀገሩ

ውሉ ፈርሱዋልና ይጮሀል በምድሩ

 

ነገን ስታልሙ ዛሬ ሄደባችሁ

ትናገራላችሁ እውነትን ጠልታችሁ

አንድ ነገር አለ እናንተ ያልገባችሁ

 

ትናንት አልፎ ዛሬን እንደው መድረሳችሁ

ጠዋትን አልፋችሁ ለዚህ ከበቃችሁ

ፋኖሱን ሳታዩት መብራት በርቶላችሁ

ምን ትመልሱ ይሆን እሱ ሲጠራችሁ

 

ማመካኘት ቀርቷል ሰው በመፈጠሩ

መመለስ ይሻላል ቀኖቹ ሳያጥሩ

አያዋጣምና በሰው መከበሩ

ለአምላክ የሚመች ጥሩ ሥራ ሥሩ

 

መሬት ለመቃረጥ ያሰባችሁ ሁሉ

ሰይጣንን ማውገዙን ኃጢያት አትበሉ

 

እናንተ ለመኖር ቤት እየሠራችሁ

የበጎቹ በረት ይፈራርስ ካላችሁ

ሰውን አታምታቱት ወንጌል አጣቅሳችሁ

ንገሩን እውነቱን እንኑር ብላችሁ

ለመኖር ነውና በሰው መፍረዳችሁ

 

ሺ ዘመን ላትኖሩ እንደው መጉዋጉዋቱ

ንስኀ ንስኀ ለምን ነው ማለቱ

ከምላስ ነበር ለካ መወትወቱ

 

በወገን ላይ ፈርዶ ቅዳሴ መግባቱ

አምላክስ ይሰማል ይደርሳል ፀሎቱ?

ፍትህ የለም ብለው በጎቹ ሲጮሁ

ሰምቶ እንዳልሰማ ምነው ዝም አላችሁ?

የማ ሥራ ኑሯል ለፍትህ መጮሁ

እናንተ ደፋሮች እኛ አፈርንባችሁ

እኛን ልታስቀኑ ደም አፍሳሽ ወዳችሁ

በደም ተለውሶ አባት ነው ካላችሁ

በቃን ተስፋ ቆረጥን ከሱዉ ጋር ይድላችሁ

 

ያለኃጢያቱ ደሙ የፈሰሰው

አውድ ምህረቱ ላይ የተንዥረገገው

ሊፋረዳችሁ ነው ደሙ እየፈላ ነው


 

ወንድወሰን ሰብሰቤ

coventry2009

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ