በልጅግ ዓሊ

“አቤት! አቤት! ደስ ማለቱ፣

አቤት! አቤት! ደስ ማለቱ፣

ያ ምንደኛ የኢህአፓ ቅጥረኛ፣

በቀይ ሽብር ተመትቶ መንገድ ላይ ሲተኛ”

- የፋሺስቶች መዝሙር 1970 ዓ.ም.

የከርቸሌ ፍርደኛ ከወትሮው ለየት ያለ ኀዘን ሰፍሮበታል። የወቅቱ አስከፊ ገጽታን የማይገነዘቡ የወንጀል እስረኞች እንኳን አዘውትረው ከሚያወሩት የሌብነት ገድል ተቆጥበዋል። ምን ትሆን ይሆን? የሚለው ጥያቄ በእያንዳንዱ እስረኛ አዕምሮ ውስጥ ይጉላላል። የልጅቷን የደስ ደስ የማያውቅ የለም። ለባሏ ያላት ፍቅር ደግሞ የተደነቀና እያንዳንዱ እስረኛ የራሱ የሚመኛት ዓይነት ሚስት ናት። እሁድ እሁድ ሕፃን ልጃቸውን ታቅፋ ለጥየቃ ሰልፍ ለመያዝ በሌሊት ነው የምትደርሰው። እሁድ ብዙ ምግብ ስለሚመጣ የምግቡን ማጣት የምታስተጓጉለው ሰኞ ሰኞ ነው። እሱም በግድ በእስረኛው ልመና።

 

ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!