በልጅግ ዓሊ

ጎረቤቴን በጣም እወድዋለሁ፣ እሱም ይወደኛል። ለብዙ ዓመታት አብረን ጎን ለጎን ኖረናል። እንመካከራለን፣ እንወያያለን፣ ችግር፣ ኀዘን፣ ደስታም አብረን እንካፈላለን። ገና ወንደላጤ ከነበርንበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ትዳር ይዘን ልጆች ወልደን እስከምናሳድግበት ድረስ ጎረቤታሞች ነን። ልጆቻችንም አብረው ነው የሚጫወቱት። የዓመት በዓልም እንደ ሀገራችን ደንብ አብረን ነው የምናሳልፋው።

 

ጎረቤቴ ያለውን ሁሉ ለኔ ከማካፈል ወደኋላ አይልም። እንደው ሞቅ ያለ ምግብ ከተሠራ እንኳ ካለኔ መብላት ይቀፈዋል። እኔም ለሱ ወደኋላ አልልም። በተቻለኝ መጠን የጠየቀኝን ለማድረግ እጥራለሁ። ብዙ ዓመታት በጉርብትና ስንኖር የከረረ ለጠብ የሚያደርሰን ነገር አላጋጠመንም። (ሙሉውን አስነብበኝ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!