የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፯

ካንስር ነው ተጠንቀቅ!
ወሬን ንፋስ ይዞት፣ እያገላበጠ አገርን ሲያዞረው፣ ከመንገድ አግኝቶህ
ጓዙን አከፋፋይ፣ ትጉህ ሠራተኛ፣ አጋሰስ ፈረሱ፣ አድርጎ ከጫነህ
ከዛ ከውትብትብ ከማይታይ ገመድ፣ ማሰሪያ ሸምቀቆ አንተን ለማላቀቅ
ማንም ኃይል የለውም፣ ጸሎት አያድንህ፣ ፀበልም አይሠራ፤ ካንሰር ነው ተጠንቀቅ!
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ወሬን ንፋስ ይዞት፣ እያገላበጠ አገርን ሲያዞረው፣ ከመንገድ አግኝቶህ
ጓዙን አከፋፋይ፣ ትጉህ ሠራተኛ፣ አጋሰስ ፈረሱ፣ አድርጎ ከጫነህ
ከዛ ከውትብትብ ከማይታይ ገመድ፣ ማሰሪያ ሸምቀቆ አንተን ለማላቀቅ
ማንም ኃይል የለውም፣ ጸሎት አያድንህ፣ ፀበልም አይሠራ፤ ካንሰር ነው ተጠንቀቅ!
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ከሳሽ ነው በብርቱ፣ ከሳሽ ነው ዲያቢሎስ፣
ሁሉንም ይከሳል
አጣልቶ በጥብጦ፣ አጋጭቶ፣ ከፋፍሎ፣
ሕዝብን ያጫርሳል
ሰው እንደበደለን፣ ሰው እንደከሰሰን፣
ሰው እንደገደለን
አርገን አንገምተው፣ እላያችን ሰፍሮ፣ ውሎ ያደረብን
ክፉ ጠላት አለን!።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
አገሬ ብትለብስም ደርባ ደራርባ
ለብዙ ዘመናት የታሪክን ካባ
እላይዋ ነተበ አስቀየመ አርጅቶ
ሠርተን ሳናድሰው ከኛ ፍቅር ጠፍቶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 3 / 5
ቀኑን ተመልክተህ እወድቃለሁ አትበል
እውነተኛ ኾኖ አይረጋም ያንተ ቃል
እሱ በፈለገው ባሻው ቦታ ወርዶ
ሚጥለውን ያውቃል የዕለቱ በረዶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
በጨመረ ቁጥር
እያንዳንዱ ቀናት
እያንዳንዱ ወራት
እያንዳንዱ ዓመታት
ከወየበው ቅጠል
ከሚረግፈው መሐል
ልቤ ድንግጥ አለ
አንዱ እኔን ይመስላል
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
አክቲቪስቱን ኪሱ፣
ጋዜጠኛን ኪሱ፣
ተቃዋሚን ኪሱ
ገጣሚውን ኪሱ፣
ከተታቸው ብሎ አንድ ሰው ነገረኝ
እሱንም አጣሁት ገብቶ ነው መሰለኝ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ለዝች ትንሽ ዕድሜ
ቤት አልሠራም ያለው
መሃላ ደርዳሪው
በአብርሃም የቀናው
በቤት ኑዛዜ ውርስ
ተጣልተው እርስ በእርስ
ሳይሠራ ባገኘው
ወንድሙን ገደለው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5
በዓለም ገበታ ከሚቀርበው ድግስ
ማንም ሰው አይችልም አንዷንም መጨረስ
ስለዚህ ሁሉንም ልትበላ አትንሰፍሰፍ
ድርሻህ ኢምንት ናት እሷን ቀምሰህ እለፍ!
ሙሉውን አስነብበኝ ...በየአውራ ጎዳናው ሲታዩ ሲሮጡ
ይመስል ነበረ ውጤት የሚያመጡ
ስንሔድ አንቸኩል እኛ ግን ቀስ ብለን
ሩጫ ሲጀመር እንቀድማቸዋለን
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ሞት ዘሪ ሞት ዘርቶ
ዘር ከዘር አባልቶ
ዘር ከዘር አራኩቶ
ይቆይ ይቆይና ዙሪያውን አዳርሶ
አይቀርም መብላቱ ከራሱ ቀንሶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...