የረቡዕ ግጥም ፪ኛ ዓመት፣ ፳፰
በሽበቴ ሳቀች
ከኔ ተነጥላ ርቃ እየሄደች
ሜዳ አልበቃ ብሏት እየፈነጠዘች
በተጨማደደ የፊቴ ገጽታ
ከከንፈሬ መሀል በወጣው ፈገግታ
ታምር እንዳየ ሰው እየተደነቀች
በወላቃ ጥርሴ በሽበቴ ሳቀች
እንዲህ የናቀችኝ እንዲህ የገረምኳት
ሌላ እንዳትመስላችሁ ወጣትነቴ ናት
ወለላዬ ከስዊድን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)



