የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ቁ. ፬
አርቆ ማስተዋል
ውሳኔን መፈጸም ወይ ትቶ መቀመጥ
የመጨረሻው ግብ ካልተጠና በቅጥ
ያረጉት ሲጎዳ የተዉት ይቆጫል
እዚህ ላይ ነው ጥቅሙ አርቆ ማስተዋል
ሙሉውን አስነብበኝ ...አርቆ ማስተዋል
ውሳኔን መፈጸም ወይ ትቶ መቀመጥ
የመጨረሻው ግብ ካልተጠና በቅጥ
ያረጉት ሲጎዳ የተዉት ይቆጫል
እዚህ ላይ ነው ጥቅሙ አርቆ ማስተዋል
ሙሉውን አስነብበኝ ...መቃጠል ነው እጣው
ዘር ኃይማኖት ይዞ ያገር ፖለቲካ
ጥላቻ እርሾ ሆኖት አብሮ ከተቦካ
ተጋግሮ አይበላም እንጀራም አይወጣው
ምጣዱ ላይ ሆኖ መቃጠል ነው እጣው
ሙሉውን አስነብበኝ ...ምክር
ሞኝ አትሁን አለኝ
ደጋግሞ መከረኝ
ብልጥ ብሆንና
ሞኝነቴን ብተው
ምንድነው የማገኝ
ምንድነው የማጣው?
ብልጥ ይሆን ሞኝ ይሆን
ራሱ መካሪው
ሙሉውን አስነብበኝ ...ክንፈሚካኤል ገረሱ
"ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል።" ይላሉ አበው፣
ጊዜ ማንሳቱ ጊዜ መጣሉ ጊዜ መስቀሉ ጊዜ ማውረዱ እሙን ነው።
ወለላዬ
ፊቱ አሸቦ መስሎ፣ እንደደነገጠ፣
ተጎልጉሎ ወጥቶ፣ ዓይኑ እንደፈጠጠ፣
ባንኮኒው ጋ ሄዶ፣ ቢራውን ጨበጠ።
የሆነውን እንጃ! ሁኔታው ያስፈራል፣
እንባው በጉንጩ ላይ፣ አቋርጦ ይፈሳል