እናታችን አሸባሪ ናት!

አልክስ አብርሃም

አባቴ ስድስት ልጆቹን ሰበሰበና የመረረ ነገር ሲኖር ብቻ የሚጠቀምበትን ሰማያዊ ሽፋን ያለውን አጀንዳውን ፊቱ ዘርግቶ ስብሰባውን ከፈተ (ስለዚህ አጀንዳው ሌላ ቀን በሰፊው እና ወራለን)! ገና ከመጀመሪያው የእለቱን አጀንዳ ሲያስተዋውቅ ነበር ሁላችንም የደነገጥነው ‹‹ ወ/ሮ ማንያህልሻል ተክሌን የሚመለከት ነው ›› ሲል ግራ ተጋባን ...... የእናታችን ስም እንዲህ እንደባቡር ሃዲድ ረዝሞ ያውም በአባታችን ሙሉውን ሲጠራ ሰምተን አናውቅም! ማኑየ ....የኔገላ ....ወለላየ ነበር በደጉ ቀን ሲጠራት! ሌላው ያጨናነቀን ነገር አባባ የእናታችንን ስም እንዲህ ያራዘመ ዋናውን ጉዳይማ እስከ ነገወዲያም አይጨርሰው የሚል ስጋ ትነበር!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ያ’ገሬና የኔ (አትክልት አሰፋ - ከቫንኩቨር)

 ያ’ገሬና የኔ

 

(አትክልት አሰፋ - ከቫንኩቨር)

 እናቴና አገሬ ሙግት ገጠሙና

ሚስቴና እናት አለም ተወዳደሩና

ልጄ እና እማምዬ ፉክክር ገቡና

    አንዱን ምረጥ ብለው ድርቅ ሲሉብኝ፤

               እናቴም ውዴ ናት፣

               ሚስቴም የኔ ፍቅር፤

  ልጄም ንጉሴ ነው፤

                 የሚጣፍጥ ከማር

የግሌ የራሴ የማ’ለውጣቸው፣

በሰላሳ ዲናር የማልቀይራቸው፤

እናት፣ ሚስት፣ ልጄ፤ ሁሉም የኔ ናቸው።

             እኔ ግን ያገሬ፤

             እኔስ የ ‘ማምዬ…

የግል ንብረት ነኝ ብዬ መለስኳቸው።

 ዲሴምበር 15/2013- ቫንኩቨር (በርናቢ)

አገርና እንጀራ (ደመቀ ከበደ-ዓባይ ዳር) [ሊነበብ የሚገባ ምርጥ ቅኔ!])

አገርና እንጀራ / መቶ ሲደመር አንድ/
/ደመቀ ከበደ - ዓባይ ዳር/

ይቺ አገር - የኛ አገር
አንዴ ´ምትቦካ - አንዴ ´ምትጋገር፤
ሲሻ ´ምትወድቅ - ሲሻ ´ምትሻገር
አንዴ ባንተ ነበር - አንዴም በኛ ነበር፤

አገር እንደ ተረት - ‹‹ተረት›› ከተባለ
ተረት ነው አገርህ - በል ተርት ምናለ፤
አገር እንቆቅልሽ - ይሁን ከተባለ
‹‹እንቆቅልሽ አገር›› - ይኸውልህ አለ፤
አገር እንደ ፈሊጥ - ምሳሌ ከሆነ
ከኛዋ አገር በላይ - ምንም ‹‹ፈሊጥ›› የለ፤

አንዱ ‹ሲተርታት› - እሳት ዳር ቁጭ ብሎ
አንዱ ይሰማዋል - ‹‹የመሰረት›› ብሎ፤
ሌላው ‹እንቆቅልሽ› - ሲያደርጋት ጨክኖ
‹ምን አውቅልህ?› ይላል - ያኛው ከጎን ሁኖ፤
ቀሪው እንደ ‹ፈሊጥ› - ቃል ሲያሳምርባት
ይኸ በምሳሌው - አለ ሲስቅባት፡፡

ይቺ አገር - የኔ አገር
ይቺ አገር - የአንተ አገር
ይቺ አገር - የአንቺ አገር
ይቺ አገር - የኛ አገር / የሁላችን አገር /
አንዴ ስትቦካ - አንዴ ስትጋገር፤
በአቡኪና ጋጋሪ - ልኳ እየተለካ
ቀድሞ ባልተፈጨ - ሊጧ እየተቦካ
አለች እስከዛሬ - ሳትመር ሳትጥም
መጋገሪያው ምጣድ - ከሙግዱ ሳይገጥም፡፡

ለዚያም ነው
የዚያኛውን አቡኪ - ይኸ እየጋገረው
ያ የጋገረውን - አንዱ እየሰበረው
በሰባራ ምጣድ - እንደ እንኩሮ እንጀራ
በመጣ፤ በሄደ - አገሬ ተጋግራ
ይህንን እንጀራ
የመጣ ጋጋሪ - ወይም ባለተራ
ለባለ አገር ሁላ - ቢያበላ፣ ቢያበላ
ጠኔ አላጠገገም - ራብም አልከላ!

ምክንያት፤
የአያቶቹን ምጣድ - አባት እየሰበረ
የአባቶቹን ምጣድ - ልጅ እየቀየረ
አገር እያቦካ - ቀዬ እየጋገረ
እልፍኝ እያበጀ - ከልካይ እያኖረ
አብሲቱን ህዝብ ግን - ይረሳው ነበረ፤

እና እንዲህ እላለሁ፤
ማነህ ባለተራ?
ምጣድ ያዘጋጀህ - ለእንጀራ ጋገራ?!
እሳት ዳር ቁጭ ብሎ - ፍሙን እየሞቀ
ከትላንት ጥጥ ላይ - የታሪክ ባዘቶ - እየፈለቀቀ
እያጠነጠነ - ሸማ እያጠለቀ
ህዝብ ይኑርልኝ ካልክ - እየፈነደቀ
በሰባራ ምጣድ - ሊጥ አታነካካ
ባለፈው ጋጋሪም - ሙያህን አትለካ
ይልቅ የእልፍኙን ሰው - ሌማቱ እንዲያረካ
በአገር ልክ ጋግር - ከህዝብ ጋር አቡካ!!
Photo: አገርና እንጀራ / መቶ ሲደመር አንድ///ደመቀ ከበደ - ዓባይ ዳር//ይቺ አገር - የኛ አገርአንዴ ´ምትቦካ - አንዴ ´ምትጋገር፤ሲሻ ´ምትወድቅ - ሲሻ ´ምትሻገርአንዴ ባንተ ነበር - አንዴም በኛ ነበር፤አገር እንደ ተረት - ‹‹ተረት›› ከተባለተረት ነው አገርህ - በል ተርት ምናለ፤አገር እንቆቅልሽ - ይሁን ከተባለ‹‹እንቆቅልሽ አገር›› - ይኸውልህ አለ፤አገር እንደ ፈሊጥ - ምሳሌ ከሆነከኛዋ አገር በላይ - ምንም ‹‹ፈሊጥ›› የለ፤አንዱ ‹ሲተርታት› - እሳት ዳር ቁጭ ብሎአንዱ ይሰማዋል - ‹‹የመሰረት›› ብሎ፤ሌላው ‹እንቆቅልሽ› - ሲያደርጋት ጨክኖ ‹ምን አውቅልህ?› ይላል - ያኛው ከጎን ሁኖ፤ቀሪው እንደ ‹ፈሊጥ› - ቃል ሲያሳምርባትይኸ በምሳሌው - አለ ሲስቅባት፡፡ይቺ አገር - የኔ አገርይቺ አገር - የአንተ አገርይቺ አገር - የአንቺ አገርይቺ አገር - የኛ አገር / የሁላችን አገር /አንዴ ስትቦካ - አንዴ ስትጋገር፤በአቡኪና ጋጋሪ - ልኳ እየተለካቀድሞ ባልተፈጨ - ሊጧ እየተቦካአለች እስከዛሬ - ሳትመር ሳትጥምመጋገሪያው ምጣድ - ከሙግዱ ሳይገጥም፡፡ለዚያም ነውየዚያኛውን አቡኪ - ይኸ እየጋገረውያ የጋገረውን - አንዱ እየሰበረውበሰባራ ምጣድ - እንደ እንኩሮ እንጀራበመጣ፤ በሄደ - አገሬ ተጋግራይህንን እንጀራየመጣ ጋጋሪ - ወይም ባለተራለባለ አገር ሁላ - ቢያበላ፣ ቢያበላጠኔ አላጠገገም - ራብም አልከላ!ምክንያት፤የአያቶቹን ምጣድ - አባት እየሰበረየአባቶቹን ምጣድ - ልጅ እየቀየረአገር እያቦካ - ቀዬ እየጋገረእልፍኝ እያበጀ - ከልካይ እያኖረአብሲቱን ህዝብ ግን - ይረሳው ነበረ፤እና እንዲህ እላለሁ፤ማነህ ባለተራ?ምጣድ ያዘጋጀህ - ለእንጀራ ጋገራ?!እሳት ዳር ቁጭ ብሎ - ፍሙን እየሞቀከትላንት ጥጥ ላይ - የታሪክ ባዘቶ - እየፈለቀቀእያጠነጠነ - ሸማ እያጠለቀህዝብ ይኑርልኝ ካልክ - እየፈነደቀበሰባራ ምጣድ - ሊጥ አታነካካባለፈው ጋጋሪም - ሙያህን አትለካይልቅ የእልፍኙን ሰው - ሌማቱ እንዲያረካበአገር ልክ ጋግር - ከህዝብ ጋር አቡካ!!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ