ኧረ እነማን ናቸው? (ጌታቸው ቃሉ)
ጌታቸው ቃሉ
ከየት ነው የመጡ ከነጥላቻቸው?
የሀገር መሪ ሆነው ሕዝብን መጥላታቸው
ምንድነው ዓላማው? ወንበር መያዛቸው
እንቅልፍ ሳይተኙ እንዲ መኖራቸው
ሀገር አይበድልም ምን አስቀይሟቸው?
ሙሉውን አስነብበኝ ...ጌታቸው ቃሉ
ከየት ነው የመጡ ከነጥላቻቸው?
የሀገር መሪ ሆነው ሕዝብን መጥላታቸው
ምንድነው ዓላማው? ወንበር መያዛቸው
እንቅልፍ ሳይተኙ እንዲ መኖራቸው
ሀገር አይበድልም ምን አስቀይሟቸው?
ሙሉውን አስነብበኝ ...ጌታቸው ቃሉ
ዘመነ ህዳሴ - ለሕዝቡ ትካዜ
ተሰማ ተደርጎ - ግፍ እንደአባዜ
ባለህዳሴዎች በልፅገናል ያሉ
ወገን በሰው ሀገር ሲሰቃይ እያዩ
ባዘን የወጣውን ጠቅልለው አሰሩ።
ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጥ ያለ፣
ከዚያ በመቀጠል ሌላ አላስከተለ?
እኔም ትእዛዙን ባለመቃወሜ፣
በቀኜ አስመትቼ፣ በግራ አስደግሜ፤
ጥቅሱን ጨረስኩና በኔ ድምዳሜ፣
ዘርሬው መጣሁኝ ደርግሜ ደርግሜ።
ቦጋለ ዳኜ - ከካሊፎርንያ
ቅኔ፤ ግጥምና የተለያዩ ድርሰቶች ባጠቃላይ ሲጠሩ 'ሥነ ጽሑፍ' ይባላሉ። ሥነጽሑፍ የሚለው ሐረግ ጥሬ ትርጉም 'የጽሑፍ ውበት' ማለት ነው። ለሥነጽሑፍ ይህ ስያሜ የተሰጠበት አንዱ ምክንያት ድርሰቶች ሲጻፉ በቃል አመራረጥ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን፤ ሥነ ጽሑፍ መዋብ እንደሚገባው ለመግለጽ ጭምር ይመስለኛል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...