ወደ ውስጥ... (አትክልት አሰፋ - ቫንኩቨር)

ዝናብ ይቀጥቅጠኝ፤ በረዶውም ይውረድ
ፀሀይም ያቃጥለኝ፤ ሰውነቴን ያንድድ፣
ናፍቆት ያስቃየኝ፤ እድሜም ይሩጥ ይለፍ፤
ሆዴን ይቦርቡረው፤ አንጀቴም ይንሰፍሰፍ፣

በሩቅ ፍቅር ራብ፤ ልታረዝ ልጠማ፣

ይንከራተት ልቤ፤ በሃሳብ ቁዘማ።

 

            ምስክር ባልሆንም፤ አጠገብሽ ሆኘ፣
            በክፉ በመጥፎ፤ ስምሽ እየናኘ
            ሃዘንሽ በርትቶ፣
            ጣርሽ ተበራክቶ፣
            የልጅ ያለህ ስትይ፤ ጆሮየ እየሰማ፣
            ፍቅርሽ ሆዴ ቀርቷል፤ ውስጤን እያደማ።
            ከጉያሽ ባልሆንም መከራሽ ሲበዛ፤
            ስቃዩ ውስጤ አለ ተቅምጧል በዛ።

 

ጉዳትሽ፣ ውርደትሽ፤ ሀዘን ሆነ ደስታ

ይደርሳል፣ ይመጣል፤ ካለሁበት ቦታ።

     ሰዎች ተገደሉ፣ ልጆችሽ ተራቡ፣

     ወጣቶችሽ ሁሉ፤ በከርቼሌ ገቡ፣

     ሙስናው በረታ፣ መብቶች ተጣሱ

     ጎሳ ተንሰራፋ፣

     ማንነትሽ ጠፋ፤

     አንችነትሽ ከፋ፤

     ፍቅር ረከሰ፣

     መተማመን ጠፍቶ፤ ፍራቻ ነገሰ።

 

ሁሉም ይዳረሳል፣ በወሬ ነጋሪ

ይመጣል ሰንጥቆ ባህርን ተሻግሮ

ነፋስንም ቀዝፎ፣ ባየር ተወርውሮ።

 

እጅግ ያሳቅቃል፤ ከርቀት ሲሰማ

ይቅርብኝ አይሉት ያንችን ነገርማ።

መዳኒት የሌለው፤ ፈውስ አይገኝለት፣

ተስፋ ብቻ ቋጥሮ አሻግሮ መመልከት።

የስቃይ ተካፋይ፣ የታሪክ መስካሪ

ሆኖ አለመገኘት፤ ያማል ውሰጥ ያደማል፣

ስቃይን ያበዛል፣ ወደ ውስጥ ይፈሳል።

 

          ግና

         

          ግና ከጎንሽ ነኝ የቅርብ ሩቅ ሆኜ

          ባህር ተሻግሬ ለመኖር ወስኜ

          ሲያምሽም ልታመም፤ ስት’ቆስይም ልቁሰል

          ላ’ይንሽ እስኪያበቃኝ ስቃዩ ይከመር

          ራብሽ ይሰማኝ፤ ጠግቤ ልታረዝ፣

          የሆንሽውን ሳልም ባሳብ ልጠማዘዝ።

ግና

 

ግና እነግርሻለሁ… ስትጮሂ እጮሃለሁ

የስቃይሽን ልክ ላ’ለም አሰማለሁ።

 

ዝናብ ይቀጥቅጠኝ፣ በረዶውም ይውረድ
ፀሀይም ያቃጥለኝ፣ ሰውነቴን ያንድድ፤
ናፍቆት ያስቃየኝ፣ እድሜም ይሩጥ፤ ይለፍ
ሆዴን ይቦርቡረው፣ አንጀቴም ይንሰፍሰፍ።…

 

ውስጤን በመሃላ ካንቺው አጣብቄ፤

ላልከዳሽ፣ ላልረሳሽ፤ ቃሌንም ጠብቄ

ልኖር ወስኛለሁ ከጉያሽ ርቄ።

 

ተጠናቀቀ ሴፕቴምበር 26/2014 8፡33 ማታ (ቫንኩቨር)

 

 

መልካም አዲስ ዓመት! (ጌታቸው አበራ)

ጌታቸው አበራ (ፒ.ዲ.ኤፍ.)
መልካም አዲስ ዓመት! - ጌታቸው አበራ Happy New Year by Getachew Abera

የታሪክ አምድ ነባራዊ፣ ምድረ-ህይወት ፍልስፍና፣

መውጣት መውረድ፣ የዓለም ሕግ፣ የተፈጥሮ ገጽ ሆነና፣

ጊዜ ክፉ፣ ጊዜ ደጉ ...፣ እጥፍ-ዘርጋ፣ ዘመም-ቀና ...፣

አንዴ ጽልመት ...፣ አንዴ ብርሃን ...፣ ባለታሪክ፣ ባለዝና፤

ስትወድቂ ...፣ ስትነሺ ...፣ በዘመናት ጉዞሽ ሂደት፣

ለዚህ ደረስሽ፤ እልልልል! ሁለት ሺ ሰባት ዓመት!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መርፌ (ወለላዬ ከስዊድን)

መርፌ (ወለላዬ ከስዊድን) Merfe by Welelaye(ወለላዬ ከስዊድን)
አንድ ቀን ተነስቶ፣
መርፌ ተቆጥቶ፣
መርፌ ተበሳጭቶ፣
አልሰጥም ያለ ቀን -
ያንን ቀዳዳውን፣
ክር አንጀቴን በላኝ -
እንጃለት መግቢያውን።

የሐመሯ ቆንጆ

Abera Lemma and yehamerewa qonjo ጋዜጠኛ አበራ ለማ ከሐመሯ ቆንጆ ጋራየወለላዬና የአበራ ለማ የግጥም ምልልስ

ደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የሬድዮ ጋዜጠኛ በነበረበት ጊዜ ወደ ጋሞጎፋ
ለሥራ ሄዶ ሳለ፣ በድንገት ካጋጠመችው የሐመር ቆንጆ ጋር የተነሳው ፎቶ ነው። ዘመኑ 1969 ዓ.ም. ሲሆን፣ ፎቶ ግራፍ አንሺው የእርዳታ ማስተባበሪያው ማንተጋፍቶት አጥናፉ ነበር። ምልልሱን ያንብቡ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሆሳዕና (ወለላዬ)

ሆሳዕና Hosaenaእንኳን አደረስዎ!

ወለላዬ ከስዊድን

ሆሳዕና

ማቴዮስ .21፥1-17

(ግጥሙን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

ወደ እየሩሳሌም ወደ ቤተፋጌ

ደርሰው ነበርና ደብረዘይት ግርጌ

በዛን ጊዜ ጌታ ደቀ መዛሙርቱን

እንዲህ ብሎ አዘዘ ጠራና ሁለቱን

ከዛ ከፊታችሁ ከምትገኝ መንደር

አህያ ታስራለች ከውርጫዋ ጋር

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እኔና አንቺ ... ፫ (ወለላዬ)

ትዳርና ስደት
ወለላዬ ከስዊድን
በሕዝብ ተጋርደን ባ'ገር ተከልለን
ለካስ እኔና አንቺ ብዙም ዕውቀት የለን።
እኔን ስመረምር አንቺን እዚህ ሳይሽ
እኔም ያን አይደለሁ፤ አንቺም ያቺ አይደለሽ።
እንዲህ ካደረገን ስደት አሸንፎ
ጭራሽ ከሚለየን ኑሮሯችንን ገፎ
ሠርግ ባንደግስም ባይረጭ አበባ
በአዲስ ትውውቅ ድጋሚ እንጋባ።
ወለላዬ ከስዊድን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. 

ለስምህ ስም ሁነው (ወለላዬ)

ወለላዬ
ከሚለጥፍብህ ከአፉ እንደመጣ
ሚሻለውን መርጠህ ለራስህ ስም አውጣ
ሺ ጨዋ ብትሆን ሚልዮን ጥንቁቅ ሰው
ሰው በሰውነትህ የሚልህ ስላለው
በችሎታህ መጠን ኪሎህን መዝነህ
ጭማሪ መጠሪያ ስም ስጠው ለራስህ
የሚጠራህ ከጠፋ አንተ ባወጣኸው
በተግባር ታይና ለስምህ ስም ሁነው!
ወለላዬ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ