… ከዚኽ ወዴት? (ክፍል አምስት - አያልሰው ደሴ)
የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አምስት (ከክፍል አራት የቀጠለ)
አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)
ሐ-፩፦ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት (ኢዴኃቅ)
በአገራችን የተደራጀ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ታሪክ የተለያዩ ፖለቲካዊ አመለካከቶችና ፍልሥፍናዎችን የሚከተሉ፣ አልፎም ተፃራሪ አስተሳሰቦችን የያዙና በተመሳሳይ የፖለቲካ ቅኝት ውስጥም ሆነው ነፍስ እስከመጠፋፋት በደረሰ ሁኔታ በምር ጠላትነት የተፈራረጁ የፖለቲካ ድርጅቶችን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ከማስቀመጥ አልፎ በጋራ ለመታገል ቆርጠው የጋራቸው የሆነ ድርጅት መሥርተው በአንድነት የታገሉበት የመጀመሪያው የጋራ የትግል መድረክ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት (ኢዴኃቅ) ነው።
ምንም እንኳን ወቅቱ ’ቀዝቃዛው ጦርነት’ የተባለው ዓለምን በአብዛኛው በሁለት አስተሳሰቦች ከፍሎ ያወዛወዘ ስሪት በሶቭየት ሕብረት ስር የነበረው የምሥራቁ ክፍል እራሱን መሸከም አቅቶት መፈረካከስ የጀመረበት ወቅት ቢሆንም፤ ደርግን ከወዳቂው ክፍል ወግኖ ያየው የምዕራብ ክፍል የመንግሥቱ ኃይለማርያምን አገዛዝ ለማስወገድ የነበረውን የቆየ ጥረት ከማፋፋም ወደኋላ አላለም። ደርግም በምሥራቅ ደጋፊዎቹ የውስጥ ማሽቆልቆል ምክንያት የሚያገኘው ዕርዳታ መቀነስ በአገሪቱ ውስጥ ከጦር ሜዳ እስከ ከተማው እያደገና እየከፋ ከመጣው ዙሪያ ጥምጥም ውጥረት ጋር ተዳምሮ በደረሰበት ጫና ተገድዶ እየተናነቀውም ቢሆን በጣም ከመሸ በኋላ አንዳንድ መሻሻሎችን ለማድረግ መሞከሩ አልቀረም። … (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)