ይድረስ ለዕጩ ’ጠቅላይ ሚንስትራችን’ ኃይሌ ገ/ሥላሴ (ነፃነት ዘገዬ)
ነፃነት ዘገዬ
የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳይ ይሁነኝ ብሎ ለሚከታተል የውስጥም ሆነ የውጭ ታዛቢ በየዕለቱ አዳዲስ አስገራሚ ነገር አያጣም። ”ቀን የሰጠው ቅል ...” እንዲሉ ጊዜ የሰጠው ሞልፋጣ ሁሉ ባልተገራ ስድ አንደበቱ ህዝብን ባገኘው አጋጣሚና መድረክ እየተነሳ ሲሳደብ መስማት ደግሞ የዘመናችን ፍሽን ሆኖ ከመገኘቱም በላይ ይህ በአሳዛኝነቱ ከሁሉም የሚበልጥ ሀገራዊ ጉዳይ ’ሃይ’ የሚለው ማጣቱ ይበልጥ ያስገርማል።
በእውነቱ እኛ ኢትዮጵያውያን በብዙ ነገር አልታደልንም። የደርግንና የወያኔን የግፍ አገዛዝ ቀንበር አለወድ በግዳችን ያው የፈረደበት ቀን ጥሎግን፣ መሸከማችን ሳያንሰን፤ በሞራልም ሆነ አቅማችን በፈቀደው ሌላ ነገር እየደገፍን እኛው በኛው ላይ ያነገሥናቸው የገዛ ልጆቻችን ተመልሰው እኛኑ ሲሳደቡና መጎናበሻ ሊያደርጉን ሲቃጡ፤ ”እባካችሁ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ!” የሚላቸው መካሪ መጥፋቱ በእጅጉ ያሳዝናል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



