የኢትዮጵያ ህዝብ ... ከዚኽ ወዴት? (አያልሰው ደሴ)
የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስር
አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)
በመሆኑም ምንም እንኳን በሁሉም ዘንድ በጎ-ፈቃድ ሊኖር ቢችልም፣ በአንድ በኩል ”ተባባሪ-አባል” በተባሉት (በአብዛኛው ፖለቲካዊ ባልሆኑ ስብስቦች) እና በኢሰዴአኃ፤ በሌላ በኩል ጉባዔውን ባዘጋጁትም ይሁን ኢሰዴአኃን በመሠረቱት ዋና ዋና በተባሉት ”አባላት” እና በኢሰዴአኃ (በአመራሩ) መኻል አለመጣጣሞችና ቅራኔዎች ብቅ ብቅ ማለት ሲጀምሩ ጊዜ አልወሰዱም።
በምክር ቤቱ አንደኛ ዓመት ዘገባ ላይ እንደተጠቀሰው በወቅቱ ኢሰዴአኃ በአባልተነት ካቀፋቸው በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ከሚገኙ አምሣ አንድ አባል ድርጅቶች በኩል ከተሳትፎ ጀምሮ ልዩ ልዩ ኃላፊነቶችን መወጣት አለመቻል፣ የድርጅት ተወካዮች አለመታመን፣ ምስጢር የማባከንና የክዳት ተግባሮችን መፈጸም፣ ከመተዳደሪያ ደንብና ከአባል ሥነ-ሥርዓትና ደንብ ውጭ በሆኑ መንገዶች ተፃራሪ ተግባሮች ላይ መሠማራት፣ ለምክር ቤቱ ሳያሳውቁ እራሳቸውን ማግልል፣ ... ወዘተ ... የመሳሰሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ገጥመውታል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



