ሙሉነህ ዮሐንስ (ከሲያትል)

ለስምንት ወራት ሙሉ በዝናብ ሲንዠቀዠቅ የነበረው የሲያትል ሰማይ ዳመናውን እየገለጠ በጉጉት ለምትጠበቀው አጭር የበጋ ፀሐይ የተመቻቸ ይመስላል። እኔም ጨቅላዋ ልጄን ከውድ ባለቤቴ ጋር ሆኜ ፀሐይ ለማሞቅ ባለኝ ጉጉት ጀንበር ሳትጠልቅ ወደቤቴ ለመድረስ የመኪና ወፈ ሰማይ ከወረረው የኢንተር ስቴት 5 ሀገር አቋራጭ አውራ ጎዳና ውስጥ እንደተዋጥኩ የእጅ ስልኬ አቃጨለች።

ዲሲ የሚኖረው ጓደኛየ ኢያሱ ጊዜ ሳያባክን “ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን መልሶ አስተካከለ” አለኝ። ከፀሐይዋ ይልቅ ይህ ጉዳይ የውስጥ ሞቅታን ጨጠረልኝ። አዎን ብርቱካን ሚደቅሳ አትላንታ ከተማ በሚደረገው የ28ኛው የሰሜን አሜሪካ የስፓርትና የባህል ፌዴሬሽን የክብር እንግዳ መሆኗ በማያዳግም ሁኔታ ተረጋገጠ። ውድ አንባብያን ብርቱካን የክብር እንግዳ እንድትሆን በፌዴሬሽኑ ቦርድ አባላት የተመረጠችው ከእስር የተፈታች ሰሞን ቢሆንም፤ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ በሆኑ የተወሰኑ ግለሰቦች ከሕገ-ደንባቸው ባፈነገጠ አሰራር ምክንያት በጉጉት ሲናፍቃት ከነበረው ኢትዮጵያዊ ማኅረሰብ ጋር የማትገናኝበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። አንባቢዎቼን ከወዲሁ ለማስገንዘብ የምወደው ይህ ጉዳይ ብዙ ቁስሌን ስለነካካ ስሜቱን ገላጭ የሆኑ ጠንከር ያሉ ቃላትን ልጠቀም ግድ ብሎኛል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ