መስፍን አማን

መቼም የአባይን መገደብ የሚቃወም ሀገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም። ለሀገራችን መልካም እናስባለን የሚሉ ሀገር ወዳድ ኃይሎች በጉዳዩ ላይ ያላቸው ተቆርቋሪነት ከወያኔ መሪዎች ቢበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም። ሁላችንም ቀን ወጥቶ በጋራና በመግባባት ሀገራችን የሀብቷ ተጠቃሚ ሆና ከማየት የበለጠ ሌላ ትልቅ ምኞት የለንም። እንደውም ብቸኛው አብዩ ምኞታችን ያ ነው።

 

ከወደ ኢትዮጵያ ሰሞኑን የሚሰማው ወሬ ሙሉ ትኩረት አባይና የትልቁ ግድብ ግንባታ ብቻ ነው (የሚሊንየም/ኅዳሴ ግድብ)። ወንዙ ብቻ ለምን ተብሎ ይመስላል ግድቡን የሚያሞካሹ ወደ ሶስት ዘፈኖች ከሰሞኑ ተለቀዋል። ኧረ እንዳውም ግድቡ ሲጠናቀቅ ሀገራችን ያሉባት ችግሮች እንደጉም ተነው እንደሚጠፉ መነገር ተጀምሮአል። እኔ ግን በሀገራችን ቅድሚያ መልስ ማግኘት ያለባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች እልባት ሳያገኙ ወደ ግድብ ግንባታው መሄድ ውጤቱ ሌላ ችግር መፈልፈል ነው የሚል አቋም ይዣለሁ። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በብዙ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተተብትባለች። እናም ለችግሮች መፍትሄ ሳንሰጥ ሌላ ነገር ማሰብ፣ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ እንደሚባለው አይነት ነገር ይሆናል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ