ፖለቲካ ሳይንስ ነው ወይ? ፖለቲካ ምሁራዊነት ያስፈልገዋል ወይ?
ፈቃዱ በቀለ
መግቢያ
በዚህ አርዕስት ላይ ለመጻፍ ከአሰብኩ ረዥም ጊዜ ሆነኝ። እንደሚታወቀው አንድ ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ ቀላል አይደለም። የመንፈስ ርጋታን የሚጠይቅ ብቻ ሳይሆን፣ ለአንባቢ የሚቀርበው ጽሁፍ ከርስ በርስ ቅራኔዎች የተላቀቀና አሳማኝ እንዲሆን አድርጎ ለመጻፍና ለማስነበብ ረዥም ጊዜን ይፈጃል። ብዙ ዕውቀትንና ምርምርን ይጠይቃል።
ተመራምሮና የተለያዩ አስተሳሰቦችን አወዳድሮና አመዛዝኖ ለአንባቢ አንድ የሚያረካና እንደመመሪያ ጥናት ለማቅረብ ረዥም ጊዜ ብቻ ሳይሆን ቢያንስ የሶስትና የአራት ሰዎችን የስራ ክፍፍል ይጠይቃል። አንድ ሰው ብቻ የሚጽፍ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ የሶስት ወር ዝግጅት ማድረግ አለበት። በተጨማሪም በኢንስቲቱሽንና በገንዘብ የሚደገፍ መሆን አለበት። በተለይም ለአገር ዕድገትና ነፃነት ተብሎ የሚጻፍ ጽሁፍና የፖለቲካ ሀተታ በአቦ ሰጡኝ የሚቀርብ ሳይሆን ብዙ ጥንቃቄን ይጠይቃል። ለአንባቢው ትክክለኛ ዕውቀትና በመረጃ የተረጋገጠ ኢንፎርሜሽን ማቅረብ ያስፈልጋል። ኢንፎርሜሽኑ ወደ አንድ ወገን ብቻ የሚያደላ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ከዚህ ስነሳ ለተለያዩ የኢትዮጵያ ድህረ-ገጾች የሚቀርቡ ኢንፎርሜሽኖች ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል። በተለይም ዕውቀትን ያዘሉ ቢሆኑ ለትግላችን ያመቻሉ። ይህን ስል ግን እኔ የተሻልኩ እጽፋለሁ ለማለት ሳይሆን፣ ቢያንስ የኔን ብቻ እንኳ ከሌሎች ኤክስፐርቶች ጋር ሳወዳድረው በብዙ እጅ ያንሳል። ከዚህ በመነሳት ወደ ዋናው ቁምነገር ልግባ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



